እንኳን ወደ ኢቫሱ የብሔራዊ ጉባኤዎች መመዝገቢያ ቅጽ በደህና መጡ

ስለ ፕሮግራሞቹ

የኢቫሱ ዋና አላማ ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት ነዉ፡፡ ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ ኢቫሱ ልዩ ልዩ ስልቶችን የሚጠቀም ሲሆን አገልጋይ መሪዎችን ማብቃት ከስልቶቹ አንዱ ነዉ፡፡ ብሔራዊ የመሪዎች ጉባኤ በሃገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተማሪ ህብረት መሪዎችን ለማስታጠቅ እና አቅጣጫ ለመስጠት የሚሰበሰብ ጉባኤ ሲሆን፤ ብሔራዊ የተልእኮ ጉባኤ ደግሞ የወንጌል ስራ በሰፊዉ ይሰራ ዘንድ በወንጌል ዙሪያ የሚሰሩ ልዩ ልዩ የተማሪ አስተማባሪዎችን (mobilizers) ለማስታጠቅና አቅጣጫ ለመስጠት የሚሰበሰብ ጉባኤ ነዉ፡፡

የምዝገባ ዝርዝር መረጃ

ብሔራዊ የተልእኮ ጉባኤ (National Mission Summit)

ብሔራዊ የመሪዎች ጉባኤ (National Leadership Summit)

ማሳሰቢያ

  • መመዝገቦትን የሚያረጋግጥ መልእክት በአስመዝጋቢዉ ሰዉ የኢሜል አድራሻ የሚላክ ይሆናል።
  • ክፍያዉን መፈጸሞትን የሚያሳይ ደረሰኝ በቴሌብር ይላካል (127 በሚል ቁጥር የጽሁፍ መልእክት ላይ ባለው ሊንክ በመግባት ደረሰኙን ማግኘት ይችላሉ)
  • ወደ ፕሮግራሙ ሲመጡ በቴሌብር የተላከዉን ደረሰኝ በማዉረድ ይዘው ይምጡ!
    ምዝገባው በአንድ ተወካይ ሰው በኩል ብቻ የሚፈፀም ይሆናል
  • ክፍያ በሙሉ በቴሌ ብር ይከናወናል
  • ተምዝግቦ የሚቀር ሰው መተካት የሚቻለው በተመሳሳይ ፆታ ከሆነ ብቻ ነው
  • ክፍያ ካልተጠናቀቀ በቀር ምዝገባው ውድቅ ይሆናል
  • የኮሌጅ ስም ዝርዝር ውስጥ ከሌለ “other” የሚለውን መርጠው ይፃፉ። የኮሌጅ ስም ሲፅፉ ግን ሙሉ ስም ከነቦታው መጻፍ እንዳይረሱ